View Screen-Reader Accessible Site

Core Beliefs

QR [View Printable Page] Home About Us Core Beliefs
TKECHURCH Core Beliefs

የእምነት አንቀጽ

1.      መጽሐፍ ቅዱስ

                     66ስቱን የብሉይና የአዲስ ኪዳን መጽሃፍትን የያዘበመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለንእንዲሁም ሊታመንበት የሚገባ የቤተክርስቲያኗ የእምነት መሰረት እርሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን። 2ጢሞ. 316-17፣ ሮሜ 15፡4፣ 2ኛ ጴጥ.1፡20፣ ዕብ. 1፡1-4

2.        እግዚአብሔር

                     ዘላለማዊየማይወሰንፍጹምየማይለወጥና ሁሉን በሚችል በአብበወልድበመንፈስ ቅዱስ  አንድ አምላክሦስት አካል  እናምናለን  ዘፍ1፡26፣ ዘዳገ.6፡4-5፣ መዝ. 89(90) 2-3፣ መዝ138(139)7-12፣ ኢሳ. 40፡28 ፣ሚልክ. 3፡6

3.        እግዚአብሔር አብ

                     እግዚአብሔር አብ ሁሉን የፈጠረ በፍቅሩ ለሰዉ ልጆች ሁሉ በገባው ቃል ኪዳን መሰረት የሰጠውን ተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደህንነት እንዳዘጋጀ እርሱን ተቀብለው ሃጢዓታቸውን ለሚናዘዙ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣን እንደሰጣቸው እናምናለንዘፍ 1፡1፤ ዘፍ 3፡15፣ ዘፍ.12፡1-3፣ ዘጸ.6፡2-3፣ ኢሳ.63፡16 ፣ 1ኛ ቆሮ.8፡6፣ ኤፌ.4፡6

4.        እግዚአብሔር ወልድ

                     ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሑር አብ ዘላለማዊ ልጅ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማሪያም መወለዱ ፍፁም ሰውና ፍፁም አምላክ መሆኑን ያለሃጢያት መኖሩንና ለሰዎችም የሃጢያትን ይቅርታ ለመስጠት ደሙን በመስቀል ላይ እንዳፈሰሰ እንደሞተና እንደተቀበረ በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነስቶ በክብር ማረጉን ለእኛም ሊያማልድ በአብ ቀኝ ተቀምጦ በሕይወት መኖሩን የቤተክርስቲያን መስራችና ራስ መሆኑን ለፍርድም እንደሚመጣ ሺህ ዓመት ከአማኞች ጋር በምድር እንደሚገዛ እናምናለን። የሐ.1፡1-14፣ የሐ.ስራ.17፡30-31፣ 1ጢሞ.3፡16፣ ዕብ.1፡8፣ ዕብ.7፡23-25፣ ዕብ.13፡8፣ ኢሳ.53፡1-12፣ ማቴ.28፡6፣ 1ጴጥ.2፡22-25፣ 2ኛቆሮ.5፡18-21፣ ኤፌ.5፡23፣ ራዕ.20፡4-5

5.        እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

                     መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ምልአተ አካል እንዳለዉና መለኮት መሆኑን ዓለምን ስለሃጥያት ስለጽድቅና ስለ ፍርድ እንደሚወቅስ በአማኝ ዉስጥ አድሮ ወደ እዉነት ሁሉ እንደሚመራቸዉ እንደሚያጽናናቸዉ የቅድስና ኑሮ ለመኖር      እንደሚያስችላቸዉ ለአገልግሎትም ሀይልንና የጸጋ ስጦታዎችን እንደሚሰጣቸዉ ዛሬም ስዎች በመንፈስ ቅዱስ ኅይል እንደሚጠመቁና በልዩ ቋንቋ (ልሳን) እንደሚናገሩ እናምናለንዘፍ 1፡2፣  የሓሥራ 5፡3-4፣ ዮሓ 14፡15-17 ፣ማር 16፡17 ፣የሓሥራ 2፡3-4፣ 8፡14-17፣ 10፡45-46 እና 19፡6-7፣ 1ኛቆሮ 12፡10-11

6.        ድነት (አዲስ ፍጥረት)

                     ሰዉ በመጀመርያ ያለኃጥያት መፈጠሩንና ነገር ግን በፍቃዱ ኃጥያት በማድረጉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቶ ሳለ ጌታ እየሱስ በፈጸመዉ ሥራ በማመን በኃጥያቱ ተፀፅቶ ንስሃ በመግባት በጸጋ ድኖ የእግዚአብሄር ልጅ በመሆንና የተሰጠዉን ደህንነት አጥብቆ በቅድስና በመያዝ የዘላለም ህይወት እንደሚወርስ እናምናለንዘፍ 3፡6፣ ዮሓ 3፡4-8፣ የሓሥራ 13፡38-39፣ ሮሜ 3፡20-26፣ 10፡9-10 እና 12፡1-2 ኤፌ 2፡8-9

7.        የክርስቶስ ዳግም ምፃት

                     የክርስቶስ ዳግም ምፃት የአማኞች ሁሉ ተስፋ በመሆኑ በህይወት ያሉና ከሙታን የሚነሱ አማኞች ጌታን በአየር እንደሚቀበሉ ከዚያም በኋላ ለዘላለም በደስታ ከእርሱ ጋርም እንደሚኖሩ እናምናለንእንዲሁም ከሺህ ዓመት መንግሥት በኋላ የማያምኑት ከሙታን ተነስተዉ በጌታ እንደሚፈረድባቸዉ እናምናለንማቴ 24፡44፣ 1ኛተሰ 4፡13-18

8.        ቅዱሳን መላእክት

                     ቅዱሳን መላእክት ሕያዋን መሆናቸዉንና ቅዱሳንንም ለመርዳት ከእግዚአብሄር ዘንድ እንደሚላኩና ጌታ ሲመጣ አብረዉ እንደሚገለጡ እናምላናለንሉቃ 1፡11-20፣ ማቴ 1፡20-22፣ 1ኛተሰ 44፡16

9.        ስይጣን

                     ሰይጣን ርኩስ መንፈስ መሆኑን የጥፋት ሁሉ ምንጭበእግዚአብሔር ላይ ያመፀ የሀሰት አባት መሆኑን በመጨረሻም ወደተዘጋጀለት የገሃነም እሳት እንደሚጣል እናምናለንዘፍ 3፡1-5፣ ኢሳ 14፡12-15፣ ዮሓ 8፡44፣ 1ኛጴጥ 5፡8፣ ራዕይ 2፡10፣ 20፡10

10.    ፍርድ

                     ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻ በክብር በሚገለጥበት ጊዜ በክርስቶስ አዳኝነት ያመኑ ከእርሱ ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማያት እንደሚኖሩና ያላመኑት ግን ለሰይጣንና ለመላዕክቱ ወደተዘጋጀ ወደዘላለም እሳት እንደሚጣሉ እናምናለን። ማቴ.25፡31-46፣ ሉቃ.13፡23-30 ፣ራዕ7፡9-17፣ 20፡10-15